አነሆ..
ዉድ የማውቃችሁ በሙሉ:: አንደምታዉቁት አንዳንዶቻችሁም አንደምትገምቱት አሜሪካ ለሚኖር ሰው ከጉዋደኛ ጋር አንደልብ ተገናኝቶ ማዉራት ወይም ወግ መጣገብ በህልም አንጂ በእዉን የሚቻል አይደለም:: በተደጋጋሚ የሁነት ና የልቦና ድርጊት አዙሪት ውስጥ መኖር የሚሰለች ብቻ ሳይሆን አስፈሪም ነው:: ለሚፈጥሩ ሰዎች አግዚአብሔር ይስጣቸውና ዛሬ ሰው ካለበት ሳይንቀሳቀስ የልቡን ሃሳብ ጀባ የሚልበት ሰሚም መልስ የሚሰጥበት ሕዝባዊ መገናኛ በሽ ነው: : በቅርቡ የጉዋደኛችንን የ ዶ/ር ሱራፌል ገብረስላሴን የአንግሊዝኛ መጣጥፎች አርሱ ባበጀው ብሎግ ማንበብ ከጀመርኩ በሁዋላ በሱው አይነት አኔም ለማዉቃቸው ሁሉ ልነግር ና ልናገር አንዲሁም ወግ ልጠርቅ ቃጣኝ:: ልቤ ተነሳሳ:: አሁን አሁን አለኝ:: ችግሩ አኔ በንግሊዝኛ ወግ አላውቅም:: ሃይ ስኩል አያለሁ ይሄ ጠፈር ይደርሳል ያስባለኝ አንግሊዝኛዬ ለመስማት ና አንብቦ ለመረዳት ወይም ከህሙማኖቼ ጋ ልግባባበት ካልሆነ በስተቀር አንዲህ ብዕሬን ሞልቼ መስክ የምወጣበት አልሆነም:: ነገር ግን ይሄው አንደምታዩት አማርኛ አሞክራለሁ:: አናም የት ሂጄ ለፈንዳ እንዳለችው አንደዚያች እንሰሳ በልቦናዬ ና በእለት ማስታውሻዬ ያኖርኩዋቸውን በርካታ ወጎች ይህን ሕዝባዊ መገናኛ በመጠቀም አነሆ ለማለት አሰብኩ:: እንግዲህ ደስ ያለው ያንብብ አኔም የስሜት ፈውስ ላግኝ..........