Wednesday, April 22, 2015

ከልቤ ማህደር

የወደፊት ሂወቴን የኑሮዬን ጎዳና
ብሩህ ላደርግ ስፍጨረጨር ላጎናፅፈው ዋስትና
ከላይ እታች ሥሯሯጥ ሌተ-ቀን ስታትር
የማይሆን ነገር ስሰራ በቁርና በቀትር
ተስፋን በውስጤ አፅድቄ እንጀራዬን ልጋግር
ሕልው መሆኔ ተሽሎኝ መጪው ጊዜዬን ላሳምር ...

አጋሮቼን ሳይ መሰሎቼን ሲለፉ ሲደክሙ ሲጥሩ
ጥቂቶችም ሲያቅታቸው መስሎ መኖር ማደሩ
ልቤ በሃዘን ፍላፃ በፍርሃት ቀስት ሲወጋ
አእምሮዬ ያለእረፍት ሲውል ሲያመሽ ሲያነጋ
የክስተቶችን ምክንያት ምርምርና ፍለጋ...

ያለሜን ጉድፍ ሰንክሳር ምንነትና ማንነት
የሁልቆ መሳፍርት ሁነት እንዴትና ወዴትነት
ማወቅ እየተሳነኝ ስተክዝና ሳቀርቅር
እንባዬም ወደ ውጭ ትቶ ወደ ውስጤ ውስጥ ሲንቆረቆር
ቆይ እስቲ...ደግሞ...በሚል ችካል ወኔዬን ስገነባ
በሕሊናዬ ስቀርፅ ተስፋን በልቤ ሳስገባ ...

ሂወቴ የነበር ቢሆንም ሕልውናዬን ሳልጠላ
ያየሁ ለት ግን ወገን በበረሃ አንገቱ ሲቀላ
የከንቱ ከንቱ እንዳለው ያ ሰው ከኖረባት በሁዋላ
እኔም ምድርን ታዘብኩዋት...ለካ እንዲህ ነች ሌላ...

ልቤ ፈራና ተባ ስሜቴን ማወቅ ተሳነኝ
ስለጠፉ እስትንፋሳት ማሰብ ዳገተኝ መሰለኝ
ይልቅ ራሴን አየሁት እንደ ውጭ ሰው ሆኜ
እናም ምንም ነኝ አልኩኝ እንደጉም የማልቅ በንኜ

ኦ! አንት የምድር የሰማይ ኃይል ሁሉን ተቆጣጣሪ
እንግዲህ ወደ አንተ እንጂ ወደሌላ አይደል የኔ ጥሪ
ወጀቡን እንዳረጋኸው በመፅሐፍ እደተፃፈው
በሰው ህሊና ገብተህ ነውጡን ይበቃል!! በለው....

Thursday, April 16, 2015




ነሐሴ 5 ቀን 1984 

የሁለተኛ መት የህክምና ትምህርት የንደኛውን ሴሚስተር ፈተና ጠናቀቅን:: ነገ ወደ ዲስበባ ለመሄድ ትኬት ቆርጫለሁ:: አንደድሮው አልቸኮልኩም:: በጉዞ በኩል በጣም የተረጋጋሁ ሰው ሆኛለሁ:: ያለፈው ሴሚስተር የጥናት ብዛትና የተደጋጋሚዎቹ ፈተናዎች ክብደት ያስከተለብኝ የመንፈስ መናወጥ ነው መሰለኝ፤ ለእረፍት ወደ ቤተሰብጋ የምሄድ በመሆኔ ምንም የተሰማኝ ነገር የለም:: ገላዬን ከታጠብኩ ከሳምንት በላይ ሆኗልና ሰውነቴ በተለይም እግሬ ይቀ**ል:: የለበስኩት ልብስም ቆሽሿል:: ወቅቱ በጅማ ክረምት የጠነከረበት ነው እየተባለ ይወራል:: እኔና አኔን መሰሎች ግን በትምህርት ባህር ውስጥ ተዘፍቀን ስለበር የክረምቱን ለውጥ ለማገናዘብ አልታደልንም:: ብቻ መሬቱ ከመጨቅየቱ የተነሳ ነጩን አዲዳስ ጫማዬን አስከማጥበው ድረስ ጥቁር ፈር ይመስል ነበር:: ዶርማችን ታጥቦ ስለማያውቅ ውጭዉን መስሏል:: ጫማዎች አዚያና አዚህ ተጥለው ይታያሉ:: ያልተነጠፉ ልጋዎች ቤቱን የእብድ ቤት ስመስለውታል፥፥ በዶርሙ ውስጥ ከተሰጡት ታጥበው ያልደረቁ ልብሶች የሚወጣው ያደረ ሽታ ላለመደው ሰው ፍንጫ ይሰነፍጣል:: እንዲህ ባለ ሁኔታ  የፒሲዋን ንደኛ ሴሚስተር አለቀ......


Thursday, April 9, 2015

ሰኔ 21 ቀን 1984 ኣም

ከጠዋቱ 3 ሰኣት 34 ደቂቃ
ይህ ዝናባማ የሆነ ሰሞን የፈተና ሰሞን ነው፥፥ ከ 25 ደቂቃ በኋላ ፊዚዮሎጂ ፈተና እንወስዳለን:: ያው ከዚህ በፊት እንዳልኩት የፊዚዮሎጂ መምህራችን ደስ አይለኝም፥፥ ይህ ስሜቴ ታዲያ በፈተናው ላይ ተፅእኖ እንዳያደርግብኝ እሰጋለሁ፥፥ ደብተሮቼን ቤተ መጽሃፍት ውስጥ ኣኑሬ ደጃፉ ላይ ጎርደድ: ጎርደድ እያልኩ ነው:: የሚቀጥሉትን ደቂቃዎች በዚሁ መልክ ለመጨረስ ማለት ነው:: ፈተናው ላይ ሂጄ ጉብ እስክል ቸኩያለሁ፥ ለመገላገል፥፥ ስለዉጤቱ ደንታ የለኝም

የሚቀጥለው ሳምንትም ቢሆን እንቅልፍ በሰላም የምተኛ ኣይመስለኝም፥፥ ምክንያቱም ፈተናው ይቀጥላል፥፥ Embryology  Biochemistry እንፈተናለን፥፥ ከሁሉም የፈራሁት ባዮኬሚስትሪን ነው፥ ብዙ ግራ የሚያጋቡ ፅንሰ-ሃሳቦችን ተምረናል:: በተለይ ግብጻዊው መምህር ከመጣና ሊፒድ ሜታቦሊዝም (Lipid Metabolism) ኣጨመላልቆ ካስተማረን ወዲህ አንብቤ በወጉ መረዳት አቅቶኛል::

ከቀኑ ስምንት ሰኣት ሃያ ደቂቃ፥
ፊዚዮሎጂ ፈተና ከባድ ኣልነበረም:: ነገር ግን ሰኣት ኣጥሮኝ ስለነበር ወደ መጨረሻ ላይ ያሉትን ጥያቄዎች በሚገባ ሳልመልሳቸው ነው የወጣሁት፥፥ ስለዚህም ቅር ብሎኛል፥፥ ኣሁን ለሌላ ፈተና ለማጥናት ገና ዝግጁ ስላልሆንኩ እስቲ የኣናቶሚ ስእሎቼን ላሰማምር……


ሙስ ሰኔ 25 ቀን 1984 ኣም ከሌሊቱ 8 ሰኣት 8 ደቂቃ:
ሊነጋ ኣራት ሰኣታት ይቀራሉ:: እስካሁን በንባብ ተግቼ የቆየሁ ቢሆንም ምንም ተጨባጭ ነገር የሰራሁ ወይም ያወቅሁ ኣልመሰለኝም፥፥ ባዮኬሚስትሪ ሊጠና ከሚገባው ግማሹን እንኩዋን ኣላዳረስኩትም::

እኔና አናቶሚ
አናቶሚ ምወደውና በሚገባም የማውቀው ትምህርት ነው………….ፕሮፌሰር ሳላህም ለኔ መልካም ግምት ያለው ይመስለኛል:: ዛሬ (በፈረንጅ ትናንትና) ቀን በኣናቶሚ ላቦራቶሪ ውስጥ በመለማመድ ላይ እያለን ሳላስበው ጮህ ብዬ ሳቄን ለቀኩት:: ፕሮፌሰር ሳላህ ኔና የኔ ቡድን የመለማመጃውን ሬሳ (Cadaver) በን ከቆምንበት ፈንጠር ብሎና ፊቱን ወደሌላ ኣቅጣጫ ኣዙሮ ስለነበር ማን አንደሳቀ ኣላወቀም፥ ግን ሳቁሰምቶ ደስ ኣላለውም:: ስለዚህም ማን አንደሳቀ ጠየቀ፥፥ ፕሮፌሰር ሳላህ ለተማሪ ክፉ ባይሆንም በቶሎ የመቆጣት ባህሪ ግን ነበረው፥፥ አኔም ሆንኩ ጉዋደኞቼ ለጥያቄው መልስ ሳንሰጥ ዝም ኣልን፥፥ የሳላህ ንዴት አየጨመረ ሄደ፥፥ የኔን ቡድን ተወና ከኛ ቀጥለው ያሉ ሁለት ቡድኖችን ማን አንደሳቀ ጠይቋቸው ከነሱ ውስጥ ኣንዱ አንዳልሆነ ቢነግሩትም ኣላመናቸውም፥፥ ሁለቱንም ቡድኖች ከላቦራቶሪው ኢንዲወጡ ኣዘዛቸው፥፥ ተቆጥቶ ኣባረራቸው፥፥ የጉዳዩ እዚህ ደረጃ መድረስ ቢያሳስበኝም ራሴን ማጋለጥ ተስኖኝ ዝም ኣልኩ፥፥ ጉዋደኞቼም ሊያጋልጡኝ ኣልሞከሩም፥፥ ይህን ድርጊት ተከትሎ ፕሮፌሰር ሳላህ ቀደም ብሎ ባቀደው መሰረት አያንዳንዳችንን የተለያዩ የሰው ሰውነት ክፍሎች ተቆራርጠው በትልልቅ ብረት ድስቶች ውስጥ ወደ ተቀመጡበት ክፍል አየወሰደ ኣጠር ያለ የቃል ፈተና ይፈትነን ጀመር፥፥ በድስቶቹ ውስጥ ማቆያ ኬሚካል ውስጥ ከተዘፈዘፉት የተበለቱ የኣካል ክፍሎች ሳላህ መርጦ እያነሳ ስለማንነታቸው ስለሚሰጡት ቅምና ላያቸው ላይ ስላሉት ነርቮች ደምስሮች ስም ይጠይቀን ነበር፥፥ የኔ ተራ ደርሶ ሳላህ ወደ ከፍሉ ይዞኝ ገባ፥፥ እዚያም ጥያቄዎችን አየጠየቀኝ ሳለ የቅድሙ ሳቅ የኔ መሆኑን ነገርኩት፥፥ በሚገርም ሁኔታ አንደጠበኩት ኣልተናደደም፥፥ ከክፍሉ ወጣና ቀደም ሲል ከኣናቶሚ ላቦራቶሪ ያባረራቸውን ሁለት ቡድኖች  ወጥቶ ጠራቸው፥፥ ለኔም ይቅርታ ኣደረገልኝ፥፥ በተረፈ ፈተናው ለኔ ቀላልና የተሳካ ነበር....