ዛሬ ማስታወሻ አላዘጋጀሁም:: ይቅርታ:: እንደሚቀጥል ግን ቃል እየገባሁ የሚቀጥሉትን ሁለት ግጥሞች እጋብዛለሁ::
ይህ የሌላ ሰው ግጥም ነው አርስቱ የሃሳብ መርከብ ነው (የገጣሚውን ስም ረስቼዋለሁ የተፃፈው ግን በ ፩፱፰፪ አ.ም. ነው )
መቁዋጫ የሌለው
የሂወት ፈተና
ሕላዌው የማያልቅ
ገቢረ ህሊና
ይጉዋዛል በፍጥነት
ሞገዱን ቀጣጥሎ
ይህ የሃሳብ መርከብ
መልህቁን መች ጥሎ
ይህ ደግሞ የኔ ግጥም ነው (2013)
ሮሮ ለ ምናብ
ዓለም ዓለም ዓለም አንቺ የኔ ዓለም
የህሊናዬ ግብር
አንች ወሰነ ሰፊ ጥግ አልባ ጠፊ ጉም
ትየለሌ ባህር
ከጥዋት አንስቶ ውድቅት እስከሚሆን
ደግሞ እስከሚነጋ
በውስጥሽ ጎዳኖች ስጉዋዝ ስብከነከን
ለህወቴ ክፍተት
ወጌሻ ፍለጋ
ማለቂያ በሌለው ድርስ ምልስ ጉዞ
አእምሮዬ ዛለ
ስጋው ሰውነቴም ወደቀ ደንዝዞ
መቆም ስላልቻለ
በውነተኛው ዓለም ነባራዊው ሂወት
የምሄድበትን
የኑሮ ሰንክሳር አቀበት ቁልቁለት
የአድሜ ጅረቴን
ልይዘው ቸገረኝ ውሉ ተዘነጋኝ
ቀልቤ ተወናብዶ
አንቺ ውስጥ ቀረሁ ግና ምን ሊጠቅመኝ
አቅሌለ ተሰዶ
No comments:
Post a Comment