ቅዳሜ ህዳር 12 ቀን 1985 አ.ም. ከምሽቱ 8 ሰዓት ከ 32 ደቂቃ
የህዳር ትዝታ
ህዳር...ህዳር.. መልካም ወር...ደስ የሚል ወር
...የፍቅር ትዝታ ወር::
አሁን ካለሁበት ይበልጥ ልጅ እግር በነበርኩበት የ1982ቱ የሐይስኩል መጨረሻ ዓመት ላይ የተከሰተውን ህዳር የማስታውሰው ለህዳር ሚካኤል እናቴ ግቢያችንን አፅድታ የከመረችውን ጥራጊ ቆሻሻ ስታነደው አየሩን በሚያጥነው ጭስ ብቻ አይደለም::
ልቤን ለመጀመሪያ ጊዜ በማላውቀው አዲስ አይነት የስሜት ዑድ ባጠነችው ቀይ ባለረዥም ፀጉር ሴት ልጅም ጭምር እንጂ......ታሪኩ
ከተሰማኝ ስሜት ዘልቆ ብዙም የተራመደ ባይሆንም ስሜቱ ራሱ ግን እንደ ጥሩ ሽቶ መአዛውን በውስጤ ተክሎ አልፉዋል:: ዛሬ ታዲያ ያን የህዳር
ስሜት የምታጭር የጅጤሳ እንስትጋ አጠር ያለ ቆይታ አጋጠመኝ::
እንዳጋጣሚ ሆኖ ዛሬ አመሻሹ ላይ የኢትዮጵያው ፓትርያርክ
አቡነ ጳውሎስ ጅጤሳ ብቅ ብለው ነበር:: ስለዚህም በርካታ የጤና ሳይንሱ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታይ ሰራተኞችና
ተማሪዎች በመመረቂያዋ ስታዲዮም ተገኝተው ነበር:: እኔም ሄጄ ነበር:: በወቅቱ ፈንጠር ብለው ወደሁዋላ ከቆሙ ስዎች ጋር
ተቀላቀልኩ:: በዚህ ሁኔታ ላይ እያለሁ ይህች ከላይ የጠቀስኩዋት የጅጤሳ እንስት አጠገቤ መጥታ ቆመች:: በአይን ባውቃትምና ሰላም ብላትም ቀረቤታ ግን
አልነበረኝም:: አሁንም ሰላም ብያት አይኔን ጳጳሱ ወዳሉበትና ለመናገሪያ ወደተዘጋጀው መድረክ አዙሬ መቆሜን ቀጠልኩ:: ወጣቷ እንስት
በራሷ አነሳሽነት ወሬ ጀመረች:: ያልጠበኩት ቢሆንም ለወሬዋ ምላሽ የመስጠት ኃላፊነት ተሰምቶኝ ይሁን በሌላ ምክንያት እኔም ማውራት
ጀመርኩ:: እሱዋ መቼም ስታወራ ድምፁዋ ዝግ ያለና በእርጋታ የሚወጣ ለስላሳና ቀጭን ነበር:: ለጆሮ ደስ የሚል...አንድ አንድ ስንባባል
የደመቀ ወሬ ውስጥ ገባን:: ከድምፁዋ ማማር በላይ ጨዋታዋ ደስ አለኝ:: እንዴ??? አልኩ በልቤ:: በቃ ልክ እሱዋን! ማለቴ
ከላይ ቀይ ባለረዥም ፀጉር ወጣት ሴት ያልኩዋትን...ያ በልቤ ውስጥ እንደ መልካም ሽቶ መአዛ ተከድኖ ተቀምጦ የነበር ትዝታ ተከፈተ::
ትክክለኛው ህዳር ህዳር ሸተተኝ: ማለቴ ፍቅሩ-ህዳር...ባለ መልካም መአዛው ህዳር...
አቡነ ጳውሎስ ወደ መድረክ ወጡና አስተማሩ
...ጮህ ብለው ሁሉ ተናገሩ ..የሰማቸው የለም:: የጅጤሳዋ እንስት ወጣት ከዚህ በፊት ታውቀኝ እንደነበረ ሆና ማውራቱዋን ቀጠለች...እንዲህ
ነችና!
ከአቡኑ ዝግጅት በሁዋላ ታዳሚው ሲበተንና ወጣቱዋ እንስትም
ጥላኝ ስትሄድ የኔ ልብ ደግሞ ተበታተነ:: ባዮኬሚስትሪ ለማጥናት ወደ ሌክቸር ሆል መሄድ ሲገባኝ ወደ ዶርሜ ሄድኩ....የተረበሸ
አእምሮ ለማስታመም........
No comments:
Post a Comment