ጥቅምት ፬ ፩፱፰፫ አ.ም.
ባለፈው አስራ አራት ብር ጠፋብኝ:: የንብረት ማቆሪያ ሳጥኔን አስተዋልኩት:: አልተሰበረም:: ቢሆንም የመጀመሪያ ጥርጣሬዬ ያነጣጠረው አንድ ቀላ ያለ ጢማም ወጣት ላይ ነው:: ጢማም ሲባል ደግሞ ቀላል ጢም አይደለም:: የጢም ጎፈሬ ብለው ይሻላል:: የሱ አልጋ ከኔ አልጋ በሶስት ረድፍ ወደ በሩ ይርቃል:: የህክምና ተማሪ አይደለም እያሉ ሌሎቹ ተማሪዎች ሲያወሩ ሰምቻለሁ:: እኔ ግን እስካሁን ቀርቤ አላነጋገርኩትም:: የተለያዩ መፍቻዎች ና ፔንሳዎች ያሉበት አነስተኛ ሳምሶናይት መሰል ቦርሳ ዘርግቶ ሲመለከት አይቼዋለሁ:: ሳጥን መስበሪያ ቢሆንስ? ሌክቸር ላይ አላየሁትም:: ማነው? ምን እያረገ ነው የሚዉለው? የሚሉ ጥያቄዎች በአእምሮዬ ይመላለሱብኛል:: ይሄው ሰው በእድሜ ከአብዛኞቻችን በለጥ የሚል ይመስላል:: በሰውነትም ቢሆን ተለቅ ያለና ፈርጣማ ይመስላል:: ስፖርት ይሰራል መሰለኝ:: ከሁለት ቀናት በፊት ከዳራሹ ጥቂት ራቅ ብላ ካለች አንዲት አጭር ቧንቧ ስር በርከክ ብሎ ገላውን ሲታጠብ አይቼዋለሁ:: በቀዝቃዛ ውሃ ማለት ነው:: ማንም ሌላ ሰው እንደዚያ ሲያደርግ አላየሁም:: በምንኖርበት የሸክላ አዳራሽ አካባቢ አመርቂ የገላ መታጠቢያ ስለሌለ ቢኖርም ዉሃ አልባ ሊሆን ስለሚችል : እኔም ሆንኩ ብዙዎቹ ሌሎች ልጆች የምንታጠበው በሳምንት አንዴ ወደከተማው በመውረድ አዌቱ የተሰኝ ገላ መታጠቢያ ማዕከል ዉስጥ ነው:: አንድ ብር ያስከፍላል:: ደግነቱ ትንሽዬ የገላ ሳሙና ይሰጣሉ::
አሁንም ስለ ቀዩ ሌባ ሊሆን የሚችል ሰው እያሰብኩ ነው:: እቺን ይወዳል! እራሴው በፈጠርኩት ጥርጣሬ ስጋት ዉስጥ ገባሁ አይደል እንዴ? ቆይ አስራ አራት ብሬን የወሰደው እሱ መሆኑን ባውቅስ? ሄጄ ብሬን ስጠኝ ልለው? ኦ...አላደርገውም! ይህን ያህል እንኩዋን ደፋር አይደለሁም:: ጭራሽ ብር እንደጠፋብኝ እንዲሰማ አልፈልግም:: በቃ! ወስዶትም ከሆነ ይጥቀመው:: እንዴ! ለነዚያ ለሐረር ልጆች አስራ አራት ብር ጠፋብኝ ብዬ ነግሬያቸዋለሁ! ድንገት ከ ሌባው ጋ ቢያወሩስ? ቶሎ ብዬ ይቅርታ አርጉልኝ ሐሰት ነው እላቸዋለሁ::
አሁን በኪሴ ዉስጥ... ሰባ የሚሆን ሳንቲም አለ:: ከቤቴ የዛሬ አስራ አምስት ቀን ስወጣ ወደ ዘጠና የሚሆኑ ብሮች ነበሩኝ:: ዘጠና ብር በብችኛ ኃላፊነት ሳስተዳድር የመጀመሪያ ግዜዬ ስለነበር ልቤ ጮቤ ረግጦ በስንት ግዜ አንደምጨርሰው ግምቱ አልነበረኝም:: ወላጆቼንም ባይ ባይ ከማለት ውጪ መቼ ተጨማሪ ገንዘብ እንደሚልኩልኝ: አንዴት አንደሚልኩልኝ ምንም አይነት ውይይት ሳላደርግ ነው ወደ ጅማ የሚገሰግሰው አውቶቡስ ላይ የተሳፈርኩት:: አሁን ስለ አስራ አራት ብሩ መጥፋት ደውዬ ልንገራቸው? ወይስ አልንገራቸው? ከነገርኩዋቸው ሌላ ጥያቄ ይመጣል:: አስራ አራት ብሩ አንዴት ጠፋ ሳይሆን ዘጠናው ብር እንዴት በ አስራ አምስት ቀን ዉስጥ አስራ አራት ብር ሆነ የሚል ነው:: እውነት ግን እንዴት በአስር ቀን ውስጥ ሰባ ስድስት ብር አጠፋሁ? ወደሁዋላ ተመልሼ አውቶቡስ ላይ ከወጣሁ ጅምሮ ያከናወንኩዋቸውን ገንዘብ ነክ ድርጊቶች ለመቃኘት ሞከርኩ:: የመጀመሪያው ወጪ አዲስ አበባ ካራ ቆሬ አካባቢ ያለ ኬላ ላይ ለበላሁት ጮርናቄ ና ለጠጣሁት ሻይ የከፈልኩት ሰባ አምስት ሳንቲም ነው:: አንድ ብር እንኩዋን አይሞላም:: ወልቂጤ ላይ ምሳ: ሰኮሩ ላይ እራት እንዲሁም አልቤርጎ...አውቶቡሱ ብልሽት ደርሶበት በመዘግየቱ ጅማ ገብቼ አላደርኩም:: በማግስቱ ረፋዱ ላይ ከሌሎች እንደኔው ፍሬሽ ማን ከሚጀምሩ ልጆች ጋር ጅማ ደረስኩ:: ጥቂት ተዋውቀንም ስለነበር ምሳ አንድ ላይ በላን: ጅማ ራስ ሆቴል:: እስከዚያ ድረስ ታዲያ ከዘጠና ብሩ ላይ ያጎደልኩት ሃያ ብር አልሞላም:: በእርግጥ በ ፐርሰንት ቢሰላ የዘጠና ብሩን ሩብ ይሆናል:: ትልቁ ወጪ የራስ ሆቴል ምሳ ሲሆን ከነ ለስላሳ መጠጡ ስድስት ብር ከሃምሳ ነበር::
በዚህ በገንዘቡ አጠፋፍ ሃሳብ ላይ እያለሁ የቤተስብ:የሰፈሬ ና የሰፈር ጉዋደኞቼ ሃሳብ መጥቶ ድቅን አለብኝ:: የናፍቆት ጎርፍ ድንገት አጥለቀለቀኝ:: ስለአንዲት የአይን ፍቅር ዉስጥ ስለገባሁባት የሰፈር ልጅ ሁሉ አሰብኩ:: ልጅቱዋ መልኩዋ ቀይ ሲሆን ደም ግባት ምን እንደሆነ ጠንቅቄ ባላውቅም ሲባል በሰማሁት እስከ ጥግ ያላት ይመስለኛል:: ረዥም ና ሉጫ ነው ፀጉሩዋ:: ታዲያ ከዚህች ቀይ ልጅ ቀጥሎ ባይኔ ሙሉ አተኩሬ ያየሁት ይሄን ቀዩን ፀጉራም ሌባ ነው:: እርግጥ ነው ሌብነቱን ገና አላረጋገጥኩም.....
ይቀጥላል..

No comments:
Post a Comment