መጋቢት ፩፮/፩፯ ቀን ፩፱፰፫ አ.ም.
ወደ ብላቴ ስንሄድ ከፍል ፭
የ ወሊሶ ትዝታ
በተማሪዎች የተሞሉት አውቶቡሶች እየተጉዋዙና ደግሞም እያረፉ ከምሽቱ አምስት ሰዓት አካባቢ ወሊሶ ከተማ ደረሱ:: ማን እንዳዘዘው ባላውቅም ወሊሶ ዉስጥ ለምሳችን ተብሎ የተዘጋጀ ምግብ ነበር:: ለእራት ሆነ:: ከተማዋ በድቅድቅ ጨለማና በፀጥታ ተውጣለች:: አልፎ አልፎ የኤሌትሪክ ግንዶች ላይ ካሉ አምፑሎች የሚወጣ የደበዘዘ ብርሃን ይታያል:: የአውቶቡሶቹ መብራትና ጉልህ ድምፅ ትንሿን ከተማ ሳያውካት አልቀረም:: እኔና ጉዋደኞቼ ከነበርንበት አውቶቡስ ጋር ከጅማ እስከ ወሊሶ ያለውን ወጣ ገባ መንገድ ከመጉዋዛችን በስተቀር የቀመስነው እህል ስላልነበር በጣም ርቦን ነበር:: ማንነታቸውን ባላውቅም የሆኑ ሰዎች እየመሩ ምግብ ወደተዘጋጀበት ቦታ ሲወስዱን በወቅቱ የነበረው ብርድ ያዘለ ነፋስ እየተንሿሿ ይገርፈን ነበር:: ከአውቶቡሱ ከወረድን በሁዋላ በአንድ መስመር ሰልፍ ይዘንና መንገዱን ተሻግረን ቀጥ ብለን ከወረድን በሁዋላ ታጥፈን ወደ አንድ የአምፑል ብርሃን ወዳለበት ቤት አመራን:: ምግብ የተዘጋጀበት ቤት ነው:: አምስት አምስት እየሆንን ያገኘነው ቦታ ላይ በመቀመጥ በትሪ ተደርጎ የቀረበልንን እንጀራ በወጥ እየተሻማን በላን::
ከምግቡ በሁዋላ ሁሉም ቀድሞ ያላሰበበት የመኝታ ጉዳይ ነበር:: ብዙም ሳይቆይ አጅበውን ከሚሄዱት ወታደሮች መረጃ መጣ:: አውቶቡሶቹ ውስጥ ቁጭ ብለን ነው ቀሪውን ሌሊት የምናሳልፈው!!! ወይኔ ጉዴ! በበኩሌ እንዴት ሆነን እንድምናድር ግራ ገባኝ:: ቁጭ ብዬ አድሬ አላውቅም:: ደነገጥኩ:: ለእንቅልፍ እንዲሆነኝ የሚያሰክር መጠጥ መጠጣት አማረኝ: ግን በዚያ ሰዓት ግሮሰሪዎችና ቡና ቤቶች በሙሉ ዝግ እንደሚሆኑ ግልፅ ነበር:: ለነገሩ አሰብኩት እንጂ ከ ስድስት ብር በስተቀር ኪሴ ውስጥ ዱዲ አልነበረም:: በእርግጥ ስድስት ብር አደንዝዞ የሚያስተኛ ያበሻ አረቄ ሊገዛ ይችላል:: (ስድስት ብሩ በቀደም ብላቴ ትሄዳላችሁ ሲባል ሁለት ሱሪዎቼንና አንድ ጫማ ሸጬ ካገኘሁት ገንዘብ ላይ የተረፈ መሆኑን ልብ በል/በይ:):
ወደ አውቶቡሱ ተመለስኩ:: መቀመጫዎች በሙሉ ተይዘው ነበር:: ቀን ስንጉዋዝ የነበርንበት አደራደር አሁን አይሰራም:: እንቅልፍ የጣላቸው ተማሪዎች የተወሰኑትን መቀመጫዎች በሞኖፖል ተጋድመውባቸዋል:: ብዙ ተማሪዎች ግን አልተኙም:: ተቀምጠው እርስ በርሳቸው ያወራሉ:: እነ ጌታቸው ና ኃይሉ አሁንም ሹፌሩ አካባቢ ተቀምጠው ሞቅ ያለ ወሬ ይዘዋል:: የነ መንግስቱን: አምሳሉንና ሚሊዮንን ድምፅ ከወደሁላ አካባቢ እሰማለሁ:: አስግድና አስፋውም እንደዚሁ መሃል አካባቢ ይሰሙኛል:: እኔ እንደቆምኩ ቀረሁ:: ምንም የምቀመጥበት ቦታ ባለመኖሩ በውስጤ ቱግ ብያለሁ:: መራመድ ራሱ አይቻልም:: የተኙ ተማሪዎች እግሮች የመረማመጃውን ቀጭን ኮሪዶር አጥረው ዘግተውታል:: የአውቶቡሱ ውስጥ የጨለመ ሲሆን ከፊል ብርሃን ደጅ ካሉት የአሌትሪክ ግንድ አምፑሎች ባውቶቡሱ መስኮቶች አልፎ ይገባል:: ከመበሳጨቴ የተነሳ ተናገር ተናገር አለኝ:: ግን የሚሰማ ሲኖር ነው እሱም:: ይህን ስረዳ ለራሴው በከባዱ እህህህህ...ብዬ ተነፈስኩ:: ራሴን አሞኝ ነበር:: የሚስማማኝ መቀመጫ ላገኝ ስላልቻልኩ እንደቆምኩ ቀረሁ:: ለነገሩ እኔም አጠፋሁ :: የተገኘው ላይ መቀመጥ ሲገባኝ የሚስማማኝ መቀመጫ መሻቴ:: የተቀመጡት ወሬያቸውን ቀጥለዋል :: አረ ተረት ተረትም የሚያወራ አለ! "ተረት ተረት" ይላል የፕሪሜዱ አስፋው " አንዳንድ አጠገቡ የነበሩ ተማሪዎች የድካም ሳቅ ይስቃሉ "ኢሂ..ኢሂ.........ኢሂ...........ሂ":: በርትቶ የላምበረት የሚል አልሰማሁም:: ራቅ ብዬ ስለነበር ተረቱ ስለምን እንደሆነ ልሰማ አልቻልኩም::
ቀስ በቀስ እንደቆምኩ ሰዓቱ ሄደ:: ወሬዎቹ አልቀነሱም:: እንዳውም ጨመሩ:: የተቀመጡ ተማሪዎች የተኙትን መቀስቀስ ጀመሩ በተራቸው ለመተኛት:: "አንተ ተነስ እንጂ አሁን ደግሞ የኔ ተራ ነው" የሚሉ ድምፆች ሰማሁ:: "ምምም......ንንንን.." ይላል የተኛ ሰው ድምፅ በእንቅልፍ ልብ አይነት:: ሰዓቱን በትክክል ባላስታውስም የሌሊቱ አጋማሽ ላይ አስፋውና ሚሊዮን በሆነ ነገር ተጣሉ:: ከተረቱ ጋ የተገናኘ ሊሆን ይችላል:: ድንገት ግርግር ሆነ:: ሊደባደቡም ተነሱ:: አስፋው እጅግ በጣም እንደተናደደ ፊቱ ላይ ያስታውቅ ነበር:: በከፊል ብርሃንም ቢሆን ፊቱ መቅላቱን አስተውያለሁ:: ከገላጋዮች ተቀላቀልኩ:: ልናገላግል በመሃል የገባነውን ሁሉ አስፋው "ዋ! ተጠንቀቁ" አለን:: እንደውም አብይንም ሊጣላው ፈለገ:: ማስረሻንም እንዲሁ:: እኔ እንደዚያ በራሴ ብስጭት ውስጥ ሆኘ የአስፋው ንግግሮች ፈገግ አስኙኝ:: የሰከረ ወይም የቀወሰ ነው የመሰለኝ:: "ዋ ይሄን ልጅ እረፍ በሉት:: እኔ ሰው እጄ ላይ አልበረክት ብሎኛል" ይልና ትንሽ ቆይቶ ደግሞ "ዋ ይሄ ልጅ በጄ ሰበብ እንዳይሆን" እያለ ይጮሃል:: እዚያ ያለነው አብዛኞችችን ቀጫጭን የነበርን ቢሆንም አስፋው ደሞ ከኛም ይቀጥን ነበር......

ግርግሩ እንደምንም በረደና ከለሊቱ አስር ሰዓት ላይ አንድ ይመቸኛል ብዬ ያሰብኩት መቀመጫ ላይ ቁጭ እንዳልኩ አሸለበኝ:: በዚያውም እንቅልፍ ወሰደኝ:: የነቃሁትም ከጠዋቱ ፩፪ ሰዓት ላይ አውቶቡሶቹ ሞተሮቻቸውን ማሞቅ ሲጀምሩ ነው:: ወሊሶ ከተማ ላይ ጎህ ቀዶ ነበር:: መጋቢት ፩፯ ቀን ከጠዋቱ ፩፪ ተኩል ሲሆን ወሊሶን ለቀቅን......
No comments:
Post a Comment