የመኝታ ክፍል ተጋሪዎቼ
በቀዩ የሸክላ አዳራሽ ዉስጥ ያድሩ የነበሩ ነገር ግን የህክምና ተማሪ ያልሆኑ ልጆች የየዲፓርትመንቶቻቸው ልጆች ወዳሉባቸው ሌሎች የሸክላ አዳራሾች እንዲዛወሩ ተደረገ:: በዚህም ምክንያት ይሄኛው የለመድኩት አዳራሽ ይበልጥ ሰፋብኝ::
ባለፈው ባዮሎጂ ቤተ ሙከራ ፀጉር በማይክሮስኮፕ ያየን ሰሞን እንደአጋጣሚ ሆኖ አብዛኞቹ ኢንስትራክተሮች የተለያዩ የቤት ስራዎችን ሰጥተውን ነበር:: የእንግሊዝኛው ኢንስትራክተር የምንፈልገውን አርስት መርጠን በእንግሊዝኛ የቃል ንግግር እንድናዘጋጅ አዝዞን ነበር:: ፊዚክስ እንደዚሁ ከሶስት ላይብረሪ ብቻ ከሚገኙ የተለያዩ መፃህፍት ዉስጥ ጥያቄዎች ሰርተን መልሱን እንድናዘጋጅ ነግሮን ነበር:: ባለው የቁጥር ውሱንነት የተነሳ መፅሃፎቹ ሰርኩለሽን ዴስክ ጀርባ ተቀምጠው በየተራ የሚወጡ ናቸው:: መፅሃፍቱን ለማግኘት አንድ ሁለት ግዜ ሞክሬ ሁሉም ቀድመው በተገኙ ሌሎች እኔን መሰሎች በመወሰዳቸው እድለኛ ልሆን አልቻልኩም:: ሂሳብም በተመሳሳይ ሁኔታ የሚሰራ ነገር ነበር::
ታዲያ እንዚህን ሁሉ በቅጡ ሳልሰራ የሳምንቱ ማብቂያ ደረሰና ያሰብኩት ሊሆን ባለመቻሉ መጠነኛ የሆነ ተስፋ መቁረጥ ተሰማኝ:: ቅዳሜ ማታ ተስፋ መቁረጥ ያመጣውን የድካም ስሜት ተጎናፅፌ አልጋዬ ላይ ተጋድሜ ሳለ በቁመናው ረዘም ያለውና ከእኔ አጠገብ የላይኛው አልጋ ላይ የሚተኛው ተማሪ መጣ:: በቅፅል ስሙ ጆን ኬኔዲ እየተባለ የሚጠራው ልጅ ነው:: ጆን ኬኔዲ እንደመጣ አልጋዬ ጫፍ ላይ ተቀመጠና በቀጥታ ወደ ቁም ነገሩ ገባ:: በዚያው ሰሞን ሁኔታዬን ሲከታተል እንደነበረና እንቅስቃሰዬ እንደቀነሰ አይነት የተሰማዉን ነገረኝ:: "ምንድን ነው? ችግር አለ እንዴ? ስለ ትናንሽ ችግሮች የምታስብ ከሆን እርሳቸው ባክህ": አለኝና: እኔ ምንም ሳልጠይቀው "ስማ! በቃ እኔ ና አንተ ዛሬ የ ጥናት ፕሮግራም እናውጣና እኔ ቢዚ አደርግሃለሁ: አለኝ:: እንዲህ ነችና! ከዚያም በፍጥነት አንድ የሆነ ፕሮግራም ነደፍን:: ከነገ ጀምሮም ፕሮግራሙን በሥራ ላይ ለማዋል ቃል ተገባባን:: ሌላም ብዙ ነገር ተነጋገርን:: ጆን ኬኔዲ ባለፈው አመት በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቨትረነሪ ሳይንስ ትምህርቱን ሲከታተል እንደቆየና እንደገና በማመልከት ሕክምና መርጦ እዚህ እንደመጣ ነገረኝ:: "የ አንድ ዓመት የስራ ልምድ ካለው ሰው ጋ ነው የማወራው አልኩ በሆዴ" ታዋቂ ሰው ያነጋገርኩ ያህል ደስ አለኝ:: ልበ ሙሉነትም ተሰማኝ:: ቀደም ሲል ይዞኝ የነበረውም ድብርት ለቀቀኝ:: ከአልጋዬ ተነሳሁና ወደ አዳራሹ መሃል ሄጄ ሰፊውን ክፍልና አልጋዎቹን አንድ ባንድ ቃኘሁዋቸው:: በዚህ ሰፊ ክፍል ውስጥ መኝታ ቤት የሚጋሩኝን ሀኪም ጨቅሎች አሰብኩአቸው:: ከተለያዩ የኢትዮጵያ ከፍሎች የመጡ ሲሆኑ ከአዲስ አበባ የሄድነው በቁጥር እንበዛለን መሰለኝ:: በመቀጠል ከጎጃም ክፍለ ሀገርም በርከት ያሉ ለጆች አሉ:: ከአዳራሹ መግቢያ በር በስተግራ ባለው ጥግ በኩል ሶስት ከ ሐረር ከተማ የመጡ ልጆች አሉ:: በጣም ይግባባሉ:: ከሐረር ልጆቹ ቀጥሎ ወደኔ አልጋ አቅጣጫ ሁለት ከወለጋ ክፍለ ሀገር የመጡ ልጆች አሉ:: ሁለቱም የታችኛው አልጋ ላይ የሚተኙ ሲሆኑ ከነሱ በላይ ካሉት ተደራቢ አልጋዎች ላይ ሁለት ከጎጃም ከፍለ ሀገር የመጡ ልጆች አሉ:: ከነሱ አጠገብ አሁንም ወደኔ አቅጣጫ ሁለት ከወሎ ክፍለ ሀገር ከደሴ የመጡ ልጆች ሲኖሩ ከነሱ ለጥቆ የ ጆን ኬኔዲ: ና ከኔው ሃይ ስኩል የመጡት ሁለት ልጆች አልጋዎች አሉ:: ከኔ በስተቀኝ አንድ ከወሊሶ ከተማ የመጣ ልጅ ሲኖር ከሱ አጠገብ ከእኤርትራ የመጣ አንድ ቀጭን ረዥም ልጅ አለ:: ከሌሎቻችን ዘግይቶ በቅርብ ነው ወደ ጅማ የመጣው:: ከሱ ቀጥሎ ደግሞ ሌላ አንድ የጎጃም ለጅ አለ......እያለ ይቀጥላል

No comments:
Post a Comment