ፈገግታ
በብሩህ አይኖች እይታ
በአእምሮ ትእዛዝ ይሁንታ
በጥርስ ድምቀት ሰጭነት
በጉንጭ ቅላት ፍካት
በከንፈር ስፋት ጥበት
በዉፍረትና በቅጥነት
በአይን ዳርቻ መሸብሸብ
ገፅ በደስታ ሲከበብ
ለተመልካች እይታ መስህብ
እንደአበባ መአዛ: እንደ አበባ ልዩ ሽታ
እንደነፋስ ሽውታ: እንደፀሃይ ብልጭታ
ፈገግታ!
ክፉን ከደግ: ሴትን ከወንድ
ክፉን ከደግ: ሴትን ከወንድ
ጨዋን ከሌባ: ጤነኛን ከእብድ
የረጋውን ከችኩል: አመለቢሱን ካመለኛው
ኡ ኡ ባዩን ከቀማኛው ከዘራፊው
'ምታግባባ በአንዲት ቅፅበት እይታ
ለልብ ለጋሽ እርጋታ...
ፈገግታ!
ፈገግታ!
ሰውን የማክበር ምልክቱ: የባልንጀርነት ስሜቱ
የመውደድ ማፍቀር ማስረጃው: የታማኝነት መግለጫው
የንፁህ ልቦና ምስክሩ: የአዲስ ፍቅር ጅምሩ
የወዳጅነት መለያው: የሂወት ምግብ ማጣፈጫው
ፈገግታ...እንደአበባ ልዩ ሽታ: እንደነፋስ ሽውታ
ለህሊና ሰጭ እርካታ: ከልብ ደራሽ ባንዳፍታ
የደስታ ምንጭ ያላት መስህብ
ፈገግታ የሂወት ምግብ
ፈገግታ!
በር ይከፈት በፈገግታ
ለእንግዳ ረዥም ቆይታ
ለመስተንግዶው ድምቀት ማማር
ለእንግዳ ምቾት ለመፍጠር
ከምግብ መጠጥ በፊት ለማስታወሻ ለትዝታ
ይቅረብ ከልብ እንደልብ : ያልተሰሰተ ፈገግታ
ፈገግታ!
ይቅረብ ከልብ እንደልብ : ያልተሰሰተ ፈገግታ
ፈገግታ!
ሰላም እንደምን አለህ: ሰላም እንደምን አለሽ
እንደምን አሉልኝ አብዬ: ደህና ውለዋል እማምዬ
እንደምንድኖት ጌታዬ
ሰላም ዋላችሁ ጉዋደኞቼ
ሰላም ዋላችሁ ጉዋደኞቼ
በጣም ደህና ነኝ ቤቶቼ
ባልንበት ሁሉ ለሰላምታ
ባልንበት ሁሉ ለሰላምታ
ይቅደመን ከልብ ፈገግታ!
ፈገግታ!
ፈገግታ!
እግዜር ይስጥልኝ: ጌታ ይባርክህ
ብዙ ያኑርህ ያሳድግህ
አመስግናለሁ አባትዬ
መርቄሻለሁ እህትዬ
ለተቀባይ ዋጋ የለው
ፈገግታዎ ከተለየው
ለፈገግታ ይኑሩ: በፈገግታም ይናገሩ
መከራ ፊትዎን ይሰውሩ
ፈገግታ...

መጋቢት 1982 አ.ም. የተፃፈ - በ ሳምሶን ኃይሌ:: ሃሳቡ እንዳለ ቢሆንም ያፃፃፍ ለውጥ ተደርጎበታል:: ከመጀመሪያው ግጥም የሄኛው በመጠን ያንሳል:: የመጀመሪያው ግጥም ግንቦት 1982 አ.ም. በአዲስ ከተማ ትምህርት ቤት በተደረገ የተማሪዎች የግጥም ውድድር ላይ ቀርቦ ሶስተኛ ደረጃ ያገኘ ሲሆን በወቅቱ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርቡዋል::
WOW samson betam des yilal, ene zare gena new yegobegnehut yanten Blog. Betam bizu tiztawoch aluh. I love the poem about Fegegta.
ReplyDeleteWOW samson betam des yilal, ene zare gena new yegobegnehut yanten Blog. Betam bizu tiztawoch aluh. I love the poem about Fegegta.
ReplyDelete