ጥቅምት ሃያ ሁለት አስራዘጠኝ መቶ ሰማንያ አራት አ.ም.
ሚድ ሴሚስተርና የአብይ ማስታወሻ
ከጥቅምት 18 እስከ 22 ባሉት ቀናት ውስጥ የ ግማሽ ሴሚስተር ፈተናዎቻችንን ወሰድን:: በእንግሊዝኛ ተጀምሮ : በኦርጋኒክ ኬሚስትሪ: ሳይኮሎጂ: ሶሺዮሎጂ :ፊዚክስ ና ማትስ ተከትሎ በ ባዮሎጂ ተጠናቀቀ:: እንግሊዝኛና ኦርጋኒክ ኬሚስትሪ ሁለቱም ከብደውኝ የነበረ ሲሆን: ሳይኮሎጂ ደግሞ ስለምወደውና በደንብ ስላነበብኩም ነው መሰል ቀሎኝ ነበር:: ፊዚክስ የጠበኩትን ያህል አልከበደኝም:: ሶሺዮሎጂ ግን የማልወደው ትምህርት ከመሆኑም ሌላ ፈተናውንም በሚገባ እንደማልወጣው አስቀድሜ ስለደመደምኩ ግዜ ሳላባክን በፍጥነት ነው ከፈተናው ከፍል የወጣሁት:: ጉዋደኞቼ ሳይገርማቸው አይቀርም:: በነገራችን ላይ በሚድ ሴሚስተር ፈተና ቀናት መሃል አንድ ምሽት የአንደኛ ሴሚስተር ውጤት ወረቀቴን ባጋጣሚ መፃሕፍ ቅዱሴን ስገልጥ አየሁት:: በጣም ማስደሰት ብቻ ሳይሆን ልክ የሌላ ሰው የሆነ ያህል አስቀናኝ:: እንደገና ደግሜ እንደማላመጣው ተሰምቶኝ ይሆናል:: 3.84 ይላል አጠቃላይ ነጥቡ.....ባጠቃላይ ስለ ሚድ ሴሚስተር ፈተና ጥሩ ስሜት አልተሰማኝም:: በደንብ አልሰራሁም:: ቢሆንም ባይሆን ብዬ ለዋናው የሴሚስተር ፈተና በርትቼ ለማጥናት በሚስጥር ለራሴ ቃል ገባሁ::
ባዮሎጂ ፈተናችንን የወሰድን እለት ከ ቀርብ ጉዋደኞቼ አንዱ የሆነው አብይ በጠየኩት መሰረት አጀንዳዬ ላይ የሚከተለውን ፅሁፍ አሰፈረ..
በመጀመሪያ ብዕሬን በግል ማስታወሻህ ላይ እንድፈትን ዕድል ስለተሰጠኝ በጣም እግዜር ይስጥልኝ:: ስዎች ከራሳቸው አፍልቀው በሚፅፉት ከገፆች አልፈው ወደ መፅሐፍት ሲሸጋገሩ መስማት እጅግ በጣም ያስደንቀኛል:: በእውነቱ
እኔ
እቺን ገፅ እንኩዋን ለመሙላት በጣም ነው የማንገራግረው::
ራሴን
ሳላስተዋውቅ: ብዙ ያወራሁ መሰለኝ:: አብይ ሕሩይ እባላለሁ:: ትውልዴ አዲስ አበባ ከፍተኛ 11 ቀበሌ 02 በተለምዶ ስሙ ሽሮ
ሜዳ አካባቢ ነው:: ጅማን መዋያ ማደሪያዬ ያደረኩት የካቲት 12 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤትን ወክለው ወደ ጅጤሳ ከመጡት “the
magnificent three” ጋር ከመስከረም ፩፮ ፩፱፰፫ ጀምሮ ነው::
ስለራሴ
ይህን ካስተዋወኩዋችሁ ዘንዳ አሁን ሰዓቱ ከምሽቱ ፮ መሆኑን ልንግራችሁ እወዳለሁ:: ዛሬ ፍፁም ነፃነት ተሰምቶኝ ነው የዋልኩት:: የ mid-semester ፈተናዎች ማሳረጊያ
የሆነው ባዮሎጂን ጨርሰን በምሽቱ የቪዲዮ ትርኢት Police Academy የተባለውን አዝናኝ ፊልም ስመለከት ነው ያመሸሁት:: በእውነቱ
ከሆነ ከፊልም አፍቃሪዎች መሃከል አንዱ ነኝ:: አላዘውትር እንጂ ፈተና በደረሰበት ሰሞን እንኩዋን ገብቼ ማየት የፊልም ፍላጎቴን
ያረካልኛል:: የዛሬውን ምሽት show ለየት ያደረገው በቪዲዮ ማሳያው አዳራሽ በኩል ሲያልፉ እንኩዋን የሚሰቀጥጣቸው ሴቶች እህቶቻችን
ሁለት ወንበር ለመጋራት መብቃታቸው ነው::
ነገ
እሁድ ነው:: ጥሩ መደበሪያ ቦታ እንደሚያስፈልገኝ በማውጠንጠን ላይ ነኝ:: እንዲያውም አንድ በጣም የልብ ጉዋደኛዬ የሆነ ከአዲስ አበባ
የመጣ ወዳጄን ጅጤሳን የማስጎብኘት ሃሳቡ መጥቶልኛል:: በዚሁ እሰናበታለሁ::
No comments:
Post a Comment